"Please wait"
እባክዎ በትዕግስት ይጠብቁ የኢንተርኔትዎ ዳካማ መሆን ነው!

Home About Us Main point Service Job Vacancy Comment

በበጀት ዓመቱ ለ117 ፕሮጀክቶች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በስራ ላይ መዋሉ ተገለጸ፡

18-05-2026 13:38pm

በበጀት ዓመቱ ለ117 ፕሮጀክቶች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በስራ ላይ መዋሉ ተገለጸ፡፡
ወልድያ፡-ሀምሌ 17/11/2017 ዓ.ም(ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን) በ2017 በጀት ዓመት ከ117 ፕሮጀክቶች መካከል 97ቱን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በስራ ላይ ማዋሉን የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪየ አስታወቀ፡፡
የመምሪያው ኃላፊ አቶ መኮነን የሱፍ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ ከተሞችን ፅዱ፣ሳቢና ማራኪ በማድረግ ለኑሮ ተስማሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በመደበኛና በኮሊደር ልማት በርካታ ስራዎች መስራት ተችሏል ብለዋል፡፡
በዞኑ ካሉ ከ117 ፕሮጀክቶች መካከል 97ቱን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ከ 600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ማድረግ ተችሏል ያሉት ኃላፊው 20 ቀሪ ፕሮጀክቶች በስራ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የተሰሩት ፕሮጀክቶች የውሃ ማስወገጃ(ማፋሰሻ) ካናል፣የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ፣የመብራትና የውሀ መስመር ዝርጋታ ፣የጠጠር መንገድ ሴራሚኮች ፣የተቋማትና የዝቅተኛ ነዋሪዎች ቤት ግንባታ እንዲሁም የአረንጓዴ ቦታና የመዝናኛ ግንባታዎች ናቸውም ብለዋል፡፡
በዞኑ ካሉት 6 ከተማ አስተዳደሮች መካከል በ 3 ከተማ አስተዳደሮች ላይ የኮሊደር ልማት እየተከናወነ መሆኑን ገልፀው በመርሳ ከተማ 4 ነጥብ 36 ኪሎ ሜትር የአስፓልት ግራና ቀኝ ማስፋፋት ስራ ከ 400 ሚሊዮን ብር በላይ በስራ ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቆቦ ከተማ 600 ሜትር የአስፓልት ግራና ቀኝ ማስፋፋት ስራ ከ 25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጎ 80 በመቶ አፈፃፀም ላይ የደረሰ ሲሆን በጋሸና ከተማ 700 ሜትር ርዝመት ያለው የአቨረንጓዴ ቦታ ማስዋብ ስራ በ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡
ሃላፊው ከ 427 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ለኮሊደር ልማት ብቻ መዋሉን አክለው ገልፀዋል፡፡
በክልልና በወረዳ በጀት በማህበረሰብ ተሳትፎ ፣ በውጭና በሀገር ውስጥ በሚኖሩ አጋር አካላት፣ከከተሞች ከራሳቸው ገቢና በመቀናጆ ፕሮጀክቶች የተሰሩ መሆናቸውንም አቶ መኮነን አብራርተዋል፡፡
በዘርፉ ለ19 ሺህ 512 የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ ዕድል ለመፍጠር በዕቅድ ተይዞ ለ 24 ሺህ 516 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡

loading

loading

loading

ይህ መረጃ 13 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇    ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form

Designed And Developed By ➜ YONAS WODAY HAILU