"Please wait"
እባክዎ በትዕግስት ይጠብቁ የኢንተርኔትዎ ዳካማ መሆን ነው!

Home About Us Main point Service Job Vacancy Comment

የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም

18-05-2026 14:57pm

የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም
የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት (የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን እና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት) በሁለተኛው ዙር (second wave) የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከተመረጡ መ/ቤቶች በመመሆናቸው ከሐምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሪፎርሙን ወደ ትግበራ ለማስገባት የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
የሪፎርሙ ቀዳሚ ግብ ዘመናዊ፣ ብቁ እና ገለልተኛ ተቋም በመገንባት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እና በዘርፋችን የሚሰጡ አገልግሎቶችን ፍሰታቸውን የጠበቁ፣ ከቢሮክራሲያዊ መጓተት የጸዱና በቴክኖሎጂ የተደገፉ በማድረግ የዜጎችን አመኔታ እና እርካታ ማሳደግ ነው። በተጨማሪም ሪፎርሙ ከፌዴራል እስከ ከተሞች ያለውን አደረጃጀት ተናባቢ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን በማድረግ ብቁ እና ትውልድን የሚሻገሩ ተቋማትን ለመገንባት ያስችላል። ይህም የተሟላ፣ የሚናበብ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ለመገንባት ያስችላል። አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በመታገዛቸው የተገልጋይ እርካታ ይጨምራል፤ የሙስና እና ብልሹ አሰራር እድሎች ይዘጋሉ። ሁሉም ተልዕኮዎች በላቀ የታማኝነት መንፈስ፣ በ"ጊዜ የለንም" ስሜት (sense of urgency) እና በውጤታማነት የሚከናወኑ ይሆናል። ይህም የመንግስትን ወጪና ጊዜ በመቆጠብ የዜጎችን እርካታ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ "ለትክክለኛው ቦታ ትክክለኛውን ባለሙያ እና አመራር" በብቃት ላይ ተመስርቶ በመመደብ፣ ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ዘመናዊ እና ውጤታማ ተቋም መገንባት ዋነኛው ግባችን ነው። ይህም ዜጎችን በላቀ ብቃት ማገልገል የሚችል እና ለሚነሱ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ ተቋማዊ አቅም ይፈጥራል። በተለይ ከመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የፖሊሲ አምዶች ስር ከተቀመጡት ተግባራት መካከል አምድ 3 የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓት መገንባትና የማስፈጸም አቅምን ማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጡት ተግባራት ዋነኛው ሲሆን፤ በዚህ አምድ ውስጥ ከተካተቱት ዋና ዋና ሥራዎች ማለትም ሥርዓተ ስልጠናዎች (Curriculum) መቅረፅ፤ የስልጠና ሞጁል ዝግጅትና አቅም ግንባታ ሥራዎች፤ የብቃት ምዘና ብሉ ፕሪንት እና የፈተና ጥያቄ ዝግጅት፤ ሠራተኞችን መመዘንና ውጤት የማሳወቅ ሥራዎች በሚቀጥሉት አራት ወራት ለማጠናቀቅ እና በምዘና ውጤት መሠረት ተከታታይ የአቅም ግንባታና የሥልጠና መርሀ ግብሮችን በጋራ መተግበር የግድ ይለናል፡፡
እነዚህን ተግባራት በተቀመጠላቸው ጊዜ እና የጥራት ደረጃ ለማዘጋጀት ከውስጥ አቅም ባሻገር ከከፍተኛ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እና በትብብር መስራት አስፈላጊ ነው። በዚህም መሰረት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተለያዩ አራት ከፍተኛ የት/ርት እና ስልጠና ተቋማት (የአዲስ አበባ ዩኒቨሪሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ እና የብቃት እና ሥራ አመራር ኢኒስቲትዩት) ጋር ዛሬ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
በቀጣይ ከፌደራል የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት ጋር በተመሳሳይ ይፈራረማል።
ዛሬ የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት አጠቃላይ ማዕቀፍ ሲሆን በቀጣይ የሚኒስቴር መ/ቤታችን እና ተጠሪ ተቋማት እንደየባህሪያቸው እና እንደየሥራ ስፋታቸው ከእነዚህ ተቋማት ጋር ውል የሚፈርሙ ይሆናል።
መረጃው Ministry of Urban and Infrastructure/Ethiopia ነው።

loading

loading

ይህ መረጃ 13 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇    ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form

Designed And Developed By ➜ YONAS WODAY HAILU