የጋዞ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት በመሰረተ ልማት ዙሪያ ከቦያ ከተማ ህብረተሰብ ጋር ውይይት አካሂዷል።ህዳር 16/2015 ዓ.ም

02-11-2025 18:27pm

በውይቱ ላይ የተገኘው የከተማው ህዝብ፣ የቀበሌው አመራርና የታዳጊው ከተማው ስራ አስኪጅና ባለሙያዎች በተገኙበት #ከተማውን ለማሳደግ የህብረተሰብ ተሳትፎወሳኝ በመሆኑ በጥሬ ገንዘብ፣ በጉልበትና በቁሳቁስ በመሰብሰብ ከተማውን ለማልማት ከህብረተሰቡ ጋር በመግባባት በጥሬ ገንዘብ ሰብስቦ አንድ ትራንስፎርመር ለማስገባት መግባባት ላይ ተደርሷል። #በከተማው ውስጥ ሰነድ አልባ የሆኑ ቦታዎችን በአጭር ቀን ውስጥ ለማጠናቀቅ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን ይህ ወርሃዊ ስብሰባም በየወሩ እንደሚቀጥል መግባባት ላይ ተድርሷል። የጋዞ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልመት ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አዳነ ታደሰ እንደገለፁት ከተማዋን ፅዱና ማራኪ ለማድረግ የከተማው ነዋሪ ያለ ማንም አስገዳጅነት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነቂስ በመውጣት ማፅዳት እንዳለበት አሳስበዋል።

ወደ ዋናው ገጽ ለመመለስ