Not ConnectionConnection refused የሰሜን ወሎ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

የሰሜን ወሎ ከተማና መሰረተ-ልማት መምሪያ

+

ድህረ-ገጹ የታየበት ብዛት

.

ከወረዳዎች የተላከ መረጃ ብዛት

.

በድህረ ገጹ ውስጥ የተላከ አስተያየት

Image Services
About Our Consulting Firm
"ከተሞችን አረንጓዴ፣ ጽዱና ለኑሮ ተስማሚ ማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ነው አወቀ ሙኔ"

የከተማ መሬት መረጃ አያያዝን ማዘመን በመጀመሩ፡ ባለጉዳዮች ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ችለዋል

አቶ ድንበሩ አክለውም በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በሁሉም ከተሞች የተጀመረውን የአሠራር ሥርዓት ወጥነት ባለው መንገድ በመዘርጋት ብልሹ አሠራርን መከላከልና የዘርፉን አደረጃጀት በማስተካከል ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የልማት ሥራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡.

በበጀት ዓመቱ ለ117 ፕሮጀክቶች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሥራ ላይ መዋሉ ተገለጸ

በበጀት ዓመቱ ለ117 ፕሮጀክቶች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሥራ ላይ መዋሉ ተገለጸ፡፡ በ2017 በጀት ዓመት ከ117 ፕሮጀክቶች መካከል 97ቱን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሥራ ላይ ማዋሉን የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪየ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ መኮንን የሱፍ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ ከተሞችን ፅዱ፣ሳቢና ማራኪ በማድረግ ለኑሮ ተስማሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በመደበኛና በኮሪደር ልማት በርካታ ስራዎች መሥራት ተችሏል ብለዋል፡፡.

(ሰሜን ወሎ ከመል- ወልዲያ ሐምሌ 4/2017 ዓ/ም)

የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።.

(ግንቦት 22/2017 ዓ.ም- ሰሜን ወሎ ከመልመ)

የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ሲቪል ምህንድስና ቡድን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።.

የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ሲቪል ምህንድስና ቡድን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

(ግንቦት 22/2017 ዓ.ም- ሰሜን ወሎ ከመልመ) የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ የሲቪል ምህንድስና ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ሊያከናውን በእቅድ ከያዛቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለከተሞችና ወረዳ ህንፃ ሹሞችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ነው በዚሁ መሰረት፦ 1.በህንፃ አዋጁ፣ ደንቡና ማስፈፀሚያ መመሪያዎች እንዲሁም በተሻሻለው የህንፃ መመሪያ 2.በነባር ግንባታ መመሪያ 3.የካሬ ሜትር መገመቻ ዋጋና ከስመ ንብረት ዝውውር መመሪያ ጋር ተጣጥሞ ስለሚሰራበት አግባብ በሚሉ ርዕሶች በመምሪያው ስር ካሉት ከሁሉም ከተሞችና ወረዳዎች ለመጡ ተሳታፊዎች በተደራጀ አግባብ ስልጠናው ተሰጥቷል።

View

የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ለ6 ከተማ አስተዳደሮች የማ/ቤታዊ አገልግሎት ስታንዳዶች ዙሪያ ለሚመለከታቸው 30 ለሚሆኑ የስራ ቡድን መሪዎችና ባሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በወልዲያ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በስልጠናው ወቅት የመምሪያው አገልግሎት አሰጣጥ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ንጉሥ መኮንን ለተሳታፊዎቹ የስልጠናውን ዓላማ ባስተላለፉበት ወቅትም "በማ/ቤዊ አገልግሎት ስታንዳርድ ዘርፍ በቂ ግንዛቤ ከማስጨበጥ በተጨማሪ ከተሞች በስታንዳርዱ መሰረት ራሳቸውን የሚመዝኑበትና የአገልግሎት አሰጣጡን ደረጃ ለማየት የዳሰሳ ጥናት ስራዎችን ለመስራት በቂ እውቀት የሚገኝበት ነው።" ብለዋል።

View

በተያዘው በጀት ዓመት ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ተመራጭ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት መፈፀማቸውን የዞኑ ከተማና መሰረተ ልማትና መምሪያ ገለጸ።

በያዘነው 2017 በጀት ዓመት ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ተመራጭ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት መፈፀማቸውን የዞኑ ከተማና መሰረተ ልማትና መምሪያ ገለጿል።የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መኮንን የሱፍ ከተሞችን ለነዋሪዎች የተመቹ ለማድረግ መሰረተ ልማትን ለማሻሻል እና የስራ እድል መፍጠሪ እንዲሆኑ ለማድረግ በተግባር የተረጋገጠ ውጤታማ ስራዎች በበጀት አመቱ 10 ወራት ተከናውነዋል ብለዋል።

View

"ባለሙያዎች ወደታች ወርደው ሲደግፉ የተሟላ እውቀት ኖሯቸው የድጋፍና ክትትል ሥራዎችን ሊያከናውኑ ይገባል።"

(ነሐሴ 28/2016 - ሰሜን ወሎ ከመል መምሪያ) በሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ከተሞችን በተሟላ እውቀት መደገፍ የሚያስችል በመሬት ልማት አስተዳደር፣ በከተማ ፕላን ዝግጅት ትግበራና አፈጻጸም፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በዜጎች ቻርተር አዘገጃጀትና በከተሞች ፈርጅ አመዳደብ ዙሪያ ከነሐሴ 25-28/2016 ዓ.ም ለ4 ቀን ስልጠና ተሰጠ።.

View

"ትልቁ ሽልማት፡ የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው፤ ዛሬ የተሰጠው ዕውቅና ትክክለኛነቱም የሚረጋገጠው፡ ተገልጋዮ ማህበረሰብ፡ በአገልግሎት አሰጣጣችን ረክቻለሁ ብሎ ምስክርነቱን ሲሰጥ ብቻ ነው"

ክቡር ዶ/ር አህመዲን መሐመድ በም/ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የቢሮው ኃላፊ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ መምሪያዎች ዕውቅና ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ከሪጆፖሊታን ከተሞች፦ 1. ባህርዳር ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ 1ኛ ደረጃና የዋንጫ ተሸላሚ 2. ደሴ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ 2ኛ ደረጃ 3. ኮምቦልቻ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ 3ኛ ደረጃ ሁነው ያጠናቀቁ ሲሆን ከዞን መምሪያዎች፦ 1. ደ/ወሎ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ 1ኛ ደረጃና የዋንጫ ተሸላሚ 2. ሰሜን ሸዋ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ 2ኛ ደረጃ 3. ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ 3ኛ ደረጃ ሁነው አጠናቀዋል።

View

የጋዞ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ፅ/ቤት በመሰረተ ልማት ዙሪያ ከቦያ ከተማ ህብረተሰብ ጋር ውይይት አካሂዷል።ህዳር 16/2015 ዓ.ም

በውይቱ ላይ የተገኘው የከተማው ህዝብ፣ የቀበሌው አመራርና የታዳጊው ከተማው ስራ አስኪጅና ባለሙያዎች በተገኙበት #ከተማውን ለማሳደግ የህብረተሰብ ተሳትፎወሳኝ በመሆኑ በጥሬ ገንዘብ፣ በጉልበትና በቁሳቁስ በመሰብሰብ ከተማውን ለማልማት ከህብረተሰቡ ጋር በመግባባት በጥሬ ገንዘብ ሰብስቦ አንድ ትራንስፎርመር ለማስገባት መግባባት ላይ ተደርሷል። #በከተማው ውስጥ ሰነድ አልባ የሆኑ ቦታዎችን በአጭር ቀን ውስጥ ለማጠናቀቅ መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን ይህ ወርሃዊ ስብሰባም በየወሩ እንደሚቀጥል መግባባት ላይ ተድርሷል። የጋዞ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልመት ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አዳነ ታደሰ እንደገለፁት ከተማዋን ፅዱና ማራኪ ለማድረግ የከተማው ነዋሪ ያለ ማንም አስገዳጅነት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነቂስ በመውጣት ማፅዳት እንዳለበት አሳስበዋል።

View

(ነሐሴ 28/2016 - ሰሜን ወሎ ከመል መምሪያ)

.

"ባለሙያዎች ወደታች ወርደው ሲደግፉ የተሟላ እውቀት ኖሯቸው የድጋፍና ክትትል ሥራዎችን ሊያከናውኑ ይገባል።በሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ከተሞችን በተሟላ እውቀት መደገፍ የሚያስችል በመሬት ልማት አስተዳደር፣ በከተማ ፕላን ዝግጅት ትግበራና አፈጻጸም፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በዜጎች ቻርተር አዘገጃጀትና በከተሞች ፈርጅ አመዳደብ ዙሪያ ከነሐሴ 25-28/2016 ዓ.ም ለ4 ቀን ስልጠና ተሰጠ።".

በበጀት ዓመቱ ለ117 ፕሮጀክቶች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሥራ ላይ መዋሉ ተገለጸ፡፡

Product Designer

በ2017 በጀት ዓመት ከ117 ፕሮጀክቶች መካከል 97ቱን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሥራ ላይ ማዋሉን የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪየ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ መኮንን የሱፍ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ ከተሞችን ፅዱ፣ሳቢና ማራኪ በማድረግ ለኑሮ ተስማሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በመደበኛና በኮሪደር ልማት በርካታ ስራዎች መሥራት ተችሏል ብለዋል፡፡.

የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። (ሰሜን ወሎ ከመል- ወልዲያ ሐምሌ 4/2017 ዓ/ም)

.

የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም የበጀት ዓመቱን ዓመታዊ የቁልፍ እና ዓበይት የሥራ አፈጻጸም ግምገማውን አካሂዷል። ግምገማው በመምሪያው ስር ባሉ ሁሉም የሥራ ቡድኖች የ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸምን የዳሰሰ ሲሆን በግምገማው ወቅት በመምሪያው ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ሊተገበሩ የሚገባቸው የማስተካከያ እርምጃዎች በዝርዝር ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ሲቪል ምህንድስና ቡድን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ። (ግንቦት 22/2017 ዓ.ም- ሰሜን ወሎ ከመልመ)

.

የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ የሲቪል ምህንድስና ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ሊያከናውን በእቅድ ከያዛቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለከተሞችና ወረዳ ህንፃ ሹሞችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ነው። በዚሁ መሰረት፦ 1.በህንፃ አዋጁ፣ ደንቡና ማስፈፀሚያ መመሪያዎች እንዲሁም በተሻሻለው የህንፃ መመሪያ 2.በነባር ግንባታ መመሪያ 3.የካሬ ሜትር መገመቻ ዋጋና ከስመ ንብረት ዝውውር መመሪያ ጋር ተጣጥሞ ስለሚሰራበት አግባብ በሚሉ ርዕሶች በመምሪያው ስር ካሉት ከሁሉም ከተሞችና ወረዳዎች ለመጡ ተሳታፊዎች በተደራጀ አግባብ ስልጠናው ተሰጥቷል።.

በተያዘው በጀት ዓመት ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ተመራጭ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት መፈፀማቸውን የዞኑ ከተማና መሰረተ ልማትና መምሪያ ገለጸ።

ወልዲያ:-ግንቦት 20/2017 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን)

በያዘነው 2017 በጀት ዓመት ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና ተመራጭ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት መፈፀማቸውን የዞኑ ከተማና መሰረተ ልማትና መምሪያ ገለጿል.የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መኮንን የሱፍ ከተሞችን ለነዋሪዎች የተመቹ ለማድረግ መሰረተ ልማትን ለማሻሻል እና የስራ እድል መፍጠሪ እንዲሆኑ ለማድረግ በተግባር የተረጋገጠ ውጤታማ ስራዎች በበጀት አመቱ 10 ወራት ተከናውነዋል ብለዋል።

ስለ አገልግሎት አሰጣጥ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ሃሳብ ካለዎት ፎርሙን በመጠቀም ይላኩ

Contact Information

Feel free to reach out with any questions about the Service

Email:

kml@gmail.com

Phone:

+251-3-33-31-14-85

Address:

Woldia

Ethiopia